ክርከብ ዝኽእል መራኸቢታት

የጋምቤላ ፕሬዘዳንት, እ አ ዘ አ በ 2003ቱ የጎሣ ፍጅት እጃቸው እንዳለበት ማመናቸው ከተዘገበ በኋላ, ከፓርቲያቸው አመራር ተነስተዋል


የቪኦኤው Peter Heinlein ከአዲስ አበባ እንደዘገበው፥ የደቡብ ጋምቤላ አመራሮች በሙስና ተዘፍቀዋል፥ የሕግ የበላይነትን አያከብሩም ተብለው ጥብቅ ክትትል ሲደረግባቸው ቆይቷል

የጋምቤላ ክልል ፕሬዘዳንት Omod Obang Olum ከሚመሩት «ከጋምቤላ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ» (ጋሕዴን) ሊቀ መንበርነታቸው መነሳታቸውን ሁለት የኢትዮጵያ የግል ጋዜጦች ዘግበውበታል። «የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ» (ጋሕዴን) የገዢው «የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር» (ኢሕአዴግ) አባል መሆኑ ይታወቃል።

Omod Obang Olum በክልሉ ፕሬዘዳንትነታቸው የመቀጠል አለመቀጠላቸው ጉዳይ ገና ግልጽ አልሆነም። በለየለት የሀገሪቱ የአንድ ብቻ ፓርቲ አሠራር ግን፥ ከመንግሥት ሥልጣን ይልቅ የፓርቲ ሥልጣን ይበልጥ ጠቃሚ ነው።

ሌሎች በርካታ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ» (ጋሕዴን) የሥራ አስፈጻሚ ኰሚቴ አባላትም ከሥራ ተባረዋል ተብሏል።

የፓርቲው ባለሥልጣናት ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ የተወሰነው፥ ለአንድ ሳምንት በዘለቀው የመንግሥቱ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ሲሆን ከተነሱ ጉዳዮች መካከል፥ ሙስና፥ ግዙፍ የእርሻ መሬቶችን ለባዕዳን ኢንቬስተሮች በኪራይ መልክ ስለሚሰጠው አጨቃጫቂው አሠራርና፥ እ አ ዘ አ በ 2003 ዓም ከ 400 በላይ የሚሆኑ የአኝዋክ ማህበረሰብ አባላት ስለተገደሉበት ድንገት ይገኙበታል።

የቪኦኤ አማርኛው ቋንቋ አገልግሎት ያነጋገራቸው የጋምቤላ ምንጮች እንደገለጹት፥ ለወትሮው በሚስጥር በሚካሄደው የግምገማ ሂደት ላይ የተሰጡ የምሥክርነት ቃሎች፥ በድብቅ በቴፕ ተቀርጸው ለሕዝብ ይፋ ከተደረጉ በኋላ ሁካታ ተፈጥሯል። በግምገማው ወቅት በሚስጥር በተቀዳው በዚያ ቴፕ ላይ፥ የክልሉ ፕሬዘዳንት Omod Obang Olum በአኝዋኰች የጅምላ ፍጅት ሚና እንደነበራቸው ሲያምኑ፥ በግድያው ወንጀል የሚጠየቁ ከሆነ ግን፥ ጉዳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊንም ይመለከታል በማለት ሲከራከሩ ይሰማሉ። በ 2003 የተገደሉትን አኝዋኮች የስም ዝርዝር ይዘው ከወታደራዊው ከፍተኛ አዛዥ ጋር ስለተገኙ፥ በፍጅቱ ይጠየቃሉ ተብለው በገምጋሚዎች በተጠየቁ ጊዜም፥ አምነዋል ይላሉ ለደህንነታቸው በመስጋት ሙሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁት አቶ Othow።

« አዎን ጊዜ ስጡኝና ለጥያቄአችሁ ነገ መልስ እሰጣለሁ አሉ። በማግስቱ ሲመለሱ በእርግጥ የስም ዝርዝሩን ሰጥቻለሁ። ነገር ግን ሰዎቹን እኔ አልገደልኩም። እኔ የስም ዝርዝሩን ሰጠሁ። ገዳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ናቸው። ምክንያቱም አኝዋኰች እንዲገደሉ ትዕዛዙን የሰጡና የወሰኑት እርሣቸው ናቸውና። ስለዚህ እኔ በጉዳዩ የምጠየቅ ከሆነ እርሣቸውም መጠየቅ አለባቸው»

አቶ Otho በተጨማሪም፥ ይህን ወንጀል ለመደበቅ ሳይሆን አይቀርም፥Omod Obang Olum ለሌላ ስድስት ወራት በሥልጣን ላይ እንዲቆየዩ የተደረገው ብለዋል።

ሙስናውን በተመለከተ ሲናገሩ ደግሞ፥ ፕሬዘዳንቱ በጋምቤላ ብቸኛው ከፍተኛ ቱጃርና፥ በአዲስ አበባ ከተማም በርሳቸውና በወንድማቸው ስም ብዙ ገንዘብ በባንክ ያስቀመጡ ባለ ብዙ ቤቶችና መኪኖች ባለቤት ናቸው። ይህ ሁሉ ከሙስና ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል። አክለውም - - - -

«አዎን ጉቦ ሲቀበሉ ቆይተዋል። የአንድ መንደር ነዋሪዎች የተፈናቀሉት በዚሁ ምክንያት ነው። ባለፈው ወር ለምሳሌ በካራቱሪ ኩባንያና በመንደርተኞቹ መካከል ውዝግብ ተነስቶ ነበር። የካራቱሪ ተወካይ በዚያን ወቅት ሲናገር፥ የመሬቱ ባለቤት እኔ ነኝ፥ በፈለግሁ ጊዜ ላስነሳችሁ መብት አለኝ። ሌላ ማንም ሥልጣን የለውም አለ። ገበሬዎቹ ሲመልሱ - እርሻ ለማስፋፋት መጣን ካላችሁ በኋላ እያካሄዳችሁ ያላችሁት መሬት ነጠቃ ነው ሲሉ ተከራክረዋል። ይህን ዓይነቱ ውዝግብ የተፈጠረው፥ Omod Obang መሬቱን ለካራቱሪ አስቀድሞ ስለሰጠ ነው»

Omod ከሌላ ሩቺን ከተባለ የሕንድ ኩባንያም በጐን ገንዘብ ይሰጠዋል። ኩባንያው፥ የመናፈሻውን ሥፍራ አጥሮ በመከለል ላይ ላለ Obang ለሚባል አስተዳዳሪ በቼክ ሳይሆን ሁለት ሚሊዮን ብር በጥሬው ቆጥሮ ሰጥቷል ይላሉ። «ኦባንግም ስልክ ለፕሬዘዳንቱ ደውሎ ምንድነው ይህን ያህል ገንዘብ የሚሰጠኝ ለምንድነው ብሎ ጠየቀ። ፕሬዘዳንቱም ዝም ብለህ ተቀበል። ካልተቀበልክ የራስህ ጉዳይ ነው - ገንዘቡን መውሰድ ካልፈለግህ አምጣው አሉት»

Human Rights Watch እ አ ዘ አ በ 2005 ዓም ያወጣው ሪፖርት፥ የኢትዮጵያ ወታደሮች በነሐሴ 2003 ያውሮፓውያኑ ዓመት በጋምቤላ አኝዋኮች ላይ ስፋት ያለው የግድያ፥ ሴቶችን አስገድዶ የመድፈርና የሰቆቃ ወንጀሎች ፈጽመዋል ሲል ከሷል። ያን ክስ ተከትሎ በመንግሥቱ የተካሄደ ምርመራ ግን፥ ባብዛኛው ወታደሮቹን ከመጥፎ ተግባር ነፃ ያወጣል።

እንዳጋጣሚ ሆኖ ደግሞ Human Rights Watch ጋምቤላን የተመለከተ ሌላ ሪፖርት በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል። ይህኛው ሪፖርት «የኢትዮጵያ መንግሥት አስገዳጅ የሠፈራ ፖሊሲ በመከተል፥ ዜጐችን ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬአቸው እያፈናቀለ መሬታቸውን ለንግድ እርሻ ያከራያል» ሲል ይከሳል። በ 70 ሺህ የሚገመቱት በዚህ መልክ ወደ ሌላ ሥፍራ ተወስደው እንዲሰፍሩ የተደረጉትም የአኝዋክ ከብት አርቢዎች ናቸው ይላል ሪፖርቱ።

ቪኦኤ ከ Human Rights Watch ተመራማሪው Ben Rawlence ጋር በቴሌፎን ባደረገው ቃለ ምልልስ፥ የክልሉ ፕሬዘዳንት Omod Obang Olum በግምገማው ወቅት ሰጡ የተባለው የእምነት ቃል፥ የኢትዮጵያ ወታደሮች እ አ ዘ አ በ 2003 ዓም በአኝዋኮች ላይ ፈጽመዋል የተባለው ፍጅት ምርመራ ጉዳይ እንደገና እንዲከፈት ማስቻል አለበት ብለዋል።

« በዚያ ጉዳይ ላይ ምርመራ እንዲደረግ በወቅቱ ጥሪ አስተላልፈናል። ስለዚህ ፕሬዘዳንቱ ባሁኑ ጊዜ የሚናገሩት ስለ እርሣቸውን ሚና ከሆነ፥ ያኔ በትክክል ምን እንደተፈጸመና በኃላፊነት የሚያስጠይቃቸው ሌሎች ካሉም ምርመራ ለማካሄድ እድል ይሰጣል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ»

የመንግሥት ኰሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምዖን አሁን ቅርብ ጊዜ በሰጡት ምላሽ - - -

«ይሄ የፈጠራ ወሬ ነው። Human Rights Watch የያዘውን የስም ማጉደፍ ዘመቻ ለማጠናከር የታቀደ ነው። ከስምንት ዓመታት በፊት በአኝዋኰችና ደገኞች መካከል ግጭት ተፈጥሮ ነበር። መንግሥት ጣልቃ በመግባት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ድምዳሜ አግኝቷል። ሁለቱ ወገኖች ዛሬ አብረው በሰላም ይኖራሉ»

እንደገና በሌላ አጋጣሚ፥ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር Donald Booth ባለሥልጣናት «ከታቀደ የከረመ» ሲሉ የገለጹትን የሁለት ቀናት የጋምቤላ ጉብኝት ባለፈው ሳምንት ውስጥ አድርገዋል። አምባሳደር Booth በጉብኝታቸው ወቅት፥ ከክልሉ ፕሬዘዳንት Omod Obang Olum ጋር ስለ ክልሉ ልማትና በኪራይ መልክ ስለሚሰጡ የንግድ እርሻ መሬቶች ጉድይ መነጋገራቸውን ከኤምባሲው የወጣ ጋዜጣዊ መግለጫ ያስረዳል። አምባሰደር Donald Booth በተጨማሪም ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኰሚሽነር /UNHCR/ ያካባቢው ተጠሪዎች ጋር መወያየታቸውን የኤምባሲው መግለጫ አብራርቷል።

XS
SM
MD
LG